
במסר שפורסם לתושבי העיר הודגש סיפורם מעורר ההשראה של נשים, גברים, ילדים וקשישים שעזבו את בתיהם וצעדו במשך חודשים ארוכים בתנאים קשים, כשהם מונעים מאמונה עמוקה ומהחלום להגיע הביתה.
על פי ההערכות, כ־4,000 מבני הקהילה נספו במהלך הדרך – במדבריות, במחנות הפליטים, ממחלות, רעב ותלאות הדרך – מבלי שזכו להגשים את חלומם להגיע לישראל.
בעירייה ציינו כי סיפורם של יהודי אתיופיה הוא חלק בלתי נפרד מהסיפור הישראלי כולו: סיפור של ציונות, אמונה, גבורה ודבקות במטרה, גם ברגעים הקשים ביותר.
עוד נמסר כי השבוע, סמוך לציון יום ירושלים, מקבל הזיכרון משמעות מיוחדת – לזכור את אלה שכל חייהם חלמו על ירושלים, צעדו לעברה, אך לא זכו לראותה.
בראשון לציון חיה כיום קהילה גדולה ומשמעותית של יוצאי אתיופיה, הנחשבת לחלק מרכזי מהמרקם החברתי, התרבותי והקהילתי של העיר.
בעירייה הדגישו כי האחריות לזכור ולהנציח את הנספים אינה שייכת רק לקהילת יוצאי אתיופיה, אלא לחברה הישראלית כולה.
“זו החובה שלנו כעיר, כחברה וכמדינה לזכור את מי שצעדו אל הארץ המובטחת באמונה גדולה ולא זכו להגיע אליה”, נמסר.
יהי זכרם ברוך.
የተከበራችህ ውድ የሪሾን ለጽዮን ነዋሪዎች፣
ዛሬ ወደ እስራኤል አገር ለመምጣት በጉዞ ላይ ሕይወታቸው ላጡ የኢትዮጵያ አይሁዳውያንን ለማሰታወስ ራሳችን ዝቅ እናደርጋለን።
በየአመቱ፣ በዚህ ሳምንት፣እኒን የሚስገርመኝ በለሊት በጨለማ በሺዎች የሚቆጠሩ ሴቶች፣ ወንዶች፣ ሕፃናት፣ አዛውንቶች እና ሙሉ ቤተሰቦች ወደማይታወቀው መንገድ የወጡት ነው።
ሁሉንም ነገር ትተው ረጅም፣ አስቸጋሪ እና ለሕይወት አስጊ የሆነ መንገድ ተጓዙ፤ ይህንንም ያደረጉት ከጥልቅ እምነት እና ከአንድ ህልም በመነሳት ነው፡ይህም ከጽዮን ለመድረስ፣ ወደ ተቀደሰችው አገራቸው መመለስ ነው።
የኢትዮጵያ አይሁዳውያን ጉዞ መልክዓ ምድራዊ ጉዞ ብቻ አልነበረም። የእምነት፣ የጽዮናዊነት፣ የጀግንነት እና ዓላማን ህልምን የመጨበጥ ጉዞ ነበር።
መንገዱን ከጀመሩት ቢተእስራኤል መካከል ወደ 4,000 የሚጠጉ ወገኖቻችን ህልማቸውን ማሳካት አልቻሉም። በመንገድ ላይ፣ በበረሃ፣ በካምፖች፣ በረሃብ፣ በበሽታ እና በመከራ ሕይወታቸው አልፏል፤ ለእስራኤል ምድር እና ለኢየሩሳሌም ያላቸው ናፍቆት እስከ መጨረሻው እስትንፋሳቸው ድረስ አብሮአቸው ነበር።
በዚህ ሳምንት የኢየሩሳሌምን ቀን እናከብራለን። ይህ ቀን ከዚህ አስደናቂ ማህበረሰብ ታሪክ ጋር በምሳሌያዊ ሁኔታ የተቆራኘ ነው - በሕይወት ዘመናቸው ዋጋ የከፈሉላትን፣ ወደ እርሷ የተጓዙትን ነገር ግን ሊያይዋት ያልታደሉትን እናስባቸዋለን።
ይህ መታሰቢያ የኢትዮጵያ ማህበረሰብ ተወላጆች ብቻ አይደለም። ይህ የሁላችንም የእስራኤል ታሪክ የማይነጠል አካል ነው፡ ወደ ቤት የመመለስ ህልሙን ያላቆመ ሕዝብ ታሪክ።
በሪሾን ለጽዮንውስጥ ትልቅ፣ ጠንካራ እና ክብር ያለው የኢትዮጵያ ተወላጆች ማህበረሰብ ይኖራል። እነሱ የከተማችን፣ የአሁኑ ጊዜያችን እና የወደፊት ህይወታችን የማይነጠል አካል ናቸው።
እንደ ከተማ፣ እንደ ማህበረሰብ እና እንደ ሀገር ማስታወስ ግዴታችን ነው። በትልቅ እምነት ወደ ተስፋይቱ ምድር የተጓዙትን ነገር ግን መድረስ ያልቻሉትን የማሰብ ኃላፊነት አለብን።
መታሰቢያቸው ለዘላለም ይኑር።
ነብሳቸውን ይማረው